የሥራ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ባሉት የጀማሪ ባለሙያ ክፍት የስራ መደቦችን በሰው ኃይል ለመሙላት ከየክልሎቹ መልምሎ በሁለት ዙር ፈተና መስጠቱ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ፈተናውን ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ሰልጣኞች በደቡብ ፖሊስ ኮሌጅ ተጨማሪ ስልጠናዎችን የምትወስዱ በመሆኑ የካቲት 4 እና 5ቀን 2015 ዓ.ም ይርጋለም ከተማ በሚገኘው የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
በተጨማሪም ስድስት ጉርድ ፎቶግራፍ እና ኦርጂናል የትምህርት ማስረጃ እንድትይዙ እየገለጽን ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን እና ስም ዝርዝራችሁን ከዚህ በታች ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን