አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 መሸጋገሪያ ድንጋጌ አንቀፅ 43(3) መሰረት አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ እቃዎች ላይ የኤክሳይስ ታክስ የሚሰላው እና የሚሰበሰበው በነባሩ አዋጅ ቁጥር 307/1995(እንደተሻሻለው) እንደሆነ ተገልጿል፡፡ አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የታክስ እና የጉምሩክ አምባሳደሮች ሆነው ተሰየሙ

Suchergebnisse

Verschachtelte Anwendungen

Asset-Herausgeber

null አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የታክስ እና የጉምሩክ አምባሳደሮች ሆነው ተሰየሙ

አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የታክስ እና የጉምሩክ አምባሳደሮች ሆነው የተሾሙ ሲሆን ከ2011 ጀምሮ በታክስ አምባሳደርነት ሲያገለግሉ የነበሩ ግለሰቦችም የክብር ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

አዲስ የተሾሙት አምባሳደሮች የሀገርን ገጽታ በመገንባት፣ የማህበረሰብን አስተሳሰብ በበጎ በመቅረጽ እና ማህበራዊ ኃላፊነቶቻቸውን በመወጣት በኩል  ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ  ናቸው፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ፣ በክብር የተሸኙትን አመስግነው አዲስ የተሾሙት የታክስ አምባሰደሮች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ  ጠይቀዋል፡፡

አዲስ የተሰየሙ የታክስ አምባሳደሮች
1.  አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ
2.  አቶ ግርማ ገ/ጻድቅ
3.  ሊቀ ትጉኃን ታጋይ ታደለ
4.  አቶ ቢኒያም በለጠ
5.  ወ/ሮ ሀናን መሀመድ
6.  ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ
7.  ዶ/ር ማሙሽ ፈንታ
8.  ዶ/ር ወዳጀነህ ማሀረነ
9.  ዶ/ር ምህረት ደበበ

በክብር የተሸኙ የታክስ አምባሳደሮች
1.  ደራሲ ጌታቸው በለጠ
2.  አርቲስት አረጋኻኝ ወራሽ
3.  አርቲስት ሀመልማል አባተ
4.  መጋቢ ኃዲስ እሸቱ አለማየሁ
5.  ሙኃዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
6.  ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
7.  አምባሰደር ሀሰን ታጁ
8.  አትሌት ጡሩነሽ ዲባባ
9.  ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ
10.  አምባሰደር ሙሉ ሰሎሞን

የጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaCustomsCommission

Asset-Herausgeber

Asset-Herausgeber

null አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 መሸጋገሪያ ድንጋጌ አንቀፅ 43(3) መሰረት አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ እቃዎች ላይ የኤክሳይስ ታክስ የሚሰላው እና የሚሰበሰበው በነባሩ አዋጅ ቁጥር 307/1995(እንደተሻሻለው) እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም አሁን ጨረታ የወጣባቸው ተሽከርካሪዎች ከተጠቀሰው የመሸጋገሪያ ጊዜ ገደብ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ስለሆኑ በአዲሱ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ መሰረት ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ የተጠየቁ ቢሆንም በተሽከርካሪዎቹ ላይ የሚፈለገውን ቀረጥ እና ታክስ ከፍለው ተሽከርካሪዎቹን መረከብ አልቻሉም፡፡

በተጨማሪም ማንኛውም አካል ከቀረጥና ታክስ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያለው እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 153-155 ባሉ ድንጋጌዎች መሰረት በየደረጃው ለተቋቋመ የአቤቱታ አጣሪ እና ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እና መደበኛ ፍርድ ቤቶች በማቅረብ መከራከር እንደሚችል በግልፅ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሰረት የተሽከርካሪዎቹ አስመጪዎች መደበኛውን የአቤቱታ አቀራረብ ሂደት ወደ ጎን በመተው ተሽከርካሪዎቹ ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ ከተለያዩ ፍርድ ቤቶች የእግድ ትዕዛዝ ያመጡ ቢሆንም ኮሚሽኑ በተሽከርካሪዎቹ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ህግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች የእግድ ትዕዛዙን አንስተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከተሽከርካሪዎቹ የሚፈለገውን የመንግስት ቀረጥና ታክስ አስመጪዎቹ ከፍለው መረከብ ባለመቻላቸው በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ 1160/2012 መሰረት እንደተተወ እቃ ተቆጥረው በኮሚሽኑ የእቃ አወጋገድ መመሪያ መሰረት ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡

ስለሆነም ኮሚሽኑ በሽያጭ ለማስወገድ በይፋ ለጨረታ ያወጣቸው ተሽከርካሪዎች በህጉ መሰረት የተፈፀመ እንጂ አንዳንድ ሚድያዎች ግለሰቦችን ዋቢ አድርገው በዘገቡት የተዛባ መረጃ መሰረት አለመሆኑ ሊታወቅ የሚገባ እና ይህንን የአንድ ወገን መረጃ ብቻ በመውሰድ መዘገብ  ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ታውቆ ሊታረም የሚገባ መሆኑን እና በቀጣይ መሰል ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በህግ አግባብ የሚጠይቅ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaCustomsCommission

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset-Herausgeber

Verschachtelte Anwendungen

Asset-Herausgeber

ጠቃሚ መረጃዎች