ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Resultados de la búsqueda

Aplicaciones anidadas

Publicador de contenidos

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ vie, 8 mar 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ mar, 27 feb 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ mié, 21 feb 2024

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡ lun, 12 feb 2024

Publicador de contenidos

Publicador de contenidos

null ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ75   ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
  ******************************************

ባሳለፍነው ሳምንት 75 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር  በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል 41 ነጥብ 7  ሚሊዮን ብር  የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 33 ነጥብ 7 በላይ  ሚሊዮን ብር  የሚያወጡ የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ  ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ድሬድዋ፣ ሀዋሳ፣  ኮምቦልቻ    ቅርንጫፍ  ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው  12 ነጥብ 9  ሚሊዮን፣ 10  ነጥብ  3 ሚሊዮን እና 4 ነጥብ 8  ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል  ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

 በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል  አልባሳት፣ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣  ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ  ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Publicador de contenidos

Aplicaciones anidadas

Publicador de contenidos

ጠቃሚ መረጃዎች