አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 መሸጋገሪያ ድንጋጌ አንቀፅ 43(3) መሰረት አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ እቃዎች ላይ የኤክሳይስ ታክስ የሚሰላው እና የሚሰበሰበው በነባሩ አዋጅ ቁጥር 307/1995(እንደተሻሻለው) እንደሆነ ተገልጿል፡፡

Résultats de recherche

Applications imbriquées

Agrégateur de contenus

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ven., 8 mars 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ mar., 27 févr. 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ mer., 21 févr. 2024

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡ lun., 12 févr. 2024

Agrégateur de contenus

Agrégateur de contenus

null አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 መሸጋገሪያ ድንጋጌ አንቀፅ 43(3) መሰረት አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ እቃዎች ላይ የኤክሳይስ ታክስ የሚሰላው እና የሚሰበሰበው በነባሩ አዋጅ ቁጥር 307/1995(እንደተሻሻለው) እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም አሁን ጨረታ የወጣባቸው ተሽከርካሪዎች ከተጠቀሰው የመሸጋገሪያ ጊዜ ገደብ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ስለሆኑ በአዲሱ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ መሰረት ቀረጥ እና ታክስ እንዲከፍሉ የተጠየቁ ቢሆንም በተሽከርካሪዎቹ ላይ የሚፈለገውን ቀረጥ እና ታክስ ከፍለው ተሽከርካሪዎቹን መረከብ አልቻሉም፡፡

በተጨማሪም ማንኛውም አካል ከቀረጥና ታክስ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያለው እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 153-155 ባሉ ድንጋጌዎች መሰረት በየደረጃው ለተቋቋመ የአቤቱታ አጣሪ እና ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እና መደበኛ ፍርድ ቤቶች በማቅረብ መከራከር እንደሚችል በግልፅ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሰረት የተሽከርካሪዎቹ አስመጪዎች መደበኛውን የአቤቱታ አቀራረብ ሂደት ወደ ጎን በመተው ተሽከርካሪዎቹ ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ ከተለያዩ ፍርድ ቤቶች የእግድ ትዕዛዝ ያመጡ ቢሆንም ኮሚሽኑ በተሽከርካሪዎቹ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ህግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች የእግድ ትዕዛዙን አንስተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ከተሽከርካሪዎቹ የሚፈለገውን የመንግስት ቀረጥና ታክስ አስመጪዎቹ ከፍለው መረከብ ባለመቻላቸው በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ 1160/2012 መሰረት እንደተተወ እቃ ተቆጥረው በኮሚሽኑ የእቃ አወጋገድ መመሪያ መሰረት ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡

ስለሆነም ኮሚሽኑ በሽያጭ ለማስወገድ በይፋ ለጨረታ ያወጣቸው ተሽከርካሪዎች በህጉ መሰረት የተፈፀመ እንጂ አንዳንድ ሚድያዎች ግለሰቦችን ዋቢ አድርገው በዘገቡት የተዛባ መረጃ መሰረት አለመሆኑ ሊታወቅ የሚገባ እና ይህንን የአንድ ወገን መረጃ ብቻ በመውሰድ መዘገብ  ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ታውቆ ሊታረም የሚገባ መሆኑን እና በቀጣይ መሰል ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በህግ አግባብ የሚጠይቅ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaCustomsCommission

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Agrégateur de contenus

Applications imbriquées

Agrégateur de contenus

ጠቃሚ መረጃዎች