የናይጀሪያ መንግስት ልኡካን ቡድን በጉምሩክ ኮሚሽን የልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት አካሄዱ

Résultats de recherche

Applications imbriquées

Agrégateur de contenus

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ven., 8 mars 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ mar., 27 févr. 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ mer., 21 févr. 2024

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡ lun., 12 févr. 2024

Agrégateur de contenus

Agrégateur de contenus

null የናይጀሪያ መንግስት ልኡካን ቡድን በጉምሩክ ኮሚሽን የልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት አካሄዱ

የናይጀሪያ መንግስት ልኡካን ቡድን በጉምሩክ ኮሚሽን የልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት አካሄዱ
**********************
የናይጀሪያ ጉምሩክ አገልግሎትን ጨምሮ ከተለያዩ  ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ  የልኡካን ቡድን አባላት በጉምሩክ ኮሚሽን  በመገኘት የልምድ ልውውጥ ያካሄዱ ሲሆን የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን የስራ እንቅስቃሴም ተመልክተዋል፡፡
የልኡካን ቡድኑ በጉምሩክ ኮሚሽን አገልግሎቱን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የተሰሩት ስራዎች አበረታች እና ተጨባጭ ልምድ ያገኙበት መሆኑን ጠቁመው በዋናው መስሪ ቤት እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የስራ ከባቢን ምቹና ማራኪ ለማድረግ የተሰራው ስራም  በተሞክሮነት የሚወስዱት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የልኡካን ቡድኑ አክለውም፣ ኮሚሽኑ ወረቀት አልባ አገልግሎትን በመተግበሩ ለደንበኞች በየትኛውም ሁኔታ እና ጊዜ አግልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ፣ ኮሚሽኑ በከፍተኛ የለውጥ ግስጋሴ ላይ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የናይጀሪያ መንግስት ልኡካን ቡድን በሁለት ቀን ቆይታቸው  የአዲስ አበባ ኤርፖርት እና በሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን የጎበኙ ሲሆን የልምድ ልውውጡ ተግባራዊ የሆኑ እውቀቶችን የቀሰሙበት እና  ስኬታማ እንደነበርም  ገልጸዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን የኮሚሽኑ የለውጥ አማካሪ አቶ መንግስቱ ተፈራ በበኩላቸው፣ በኮሚሽኑ  ባለፉት ሶስት ዓመታት መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው በቀጣይም የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ የሚያዘመኑን ኮሚሽኑን ብቁ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Agrégateur de contenus

Applications imbriquées

Agrégateur de contenus

ጠቃሚ መረጃዎች