ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡ - የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

Résultats de recherche

Applications imbriquées

Agrégateur de contenus

null ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ.ም)

የጉምሩክ ኮሚሽን የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚህ የግምገማ መድረክ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው በገቢ አሰባሰቡ የተመዘገበው ውጤትም ስኬታማ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

በ2016 የመጀመሪያው ግማሽ የበጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ አርእስቶች 103 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እቅድ የነበረ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ  97 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንም ገልፀዋል፡፡

ገቢው የተሰበሰበው ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስ እና ከሌሎች ታክስ እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ነው ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ ካለፈው የበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም በ9.9 ቢሊዮን ብር (11.42 በመቶ) ብልጫ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡
የኮሚሽኑ የስትራቴጂክ ፕላን እና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ዱፌራ የኮሚሽኑን የ2016 ግማሽ በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission

Agrégateur de contenus

Agrégateur de contenus

ዜና

  • ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ven., 8 mars 2024
ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
  • ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ mar., 27 févr. 2024
ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
  • ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ mer., 21 févr. 2024
ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Agrégateur de contenus

Applications imbriquées

Agrégateur de contenus

ጠቃሚ መረጃዎች