ጉምሩክ ኮሚሽን
ጉምሩክ ኮምሽን በኢትዩጵያ ተቋማት ታሪክ እድሜ ጠገብ ከሚባሉት መካከል የሚመደብ ነዉ፡፡ በ1881 ዓ.ም ለገንዘብና ግምጃ ቤት፤ በ1916 ዓ.ም ለንግድ ሚኒስተር እንዲሁም በ1985 ዓ.ም በገቢያዎች ሚኒስተር በአወጅ ቁጥር 60/1989 በገቢዎች ቦርድ በኩል ሲተዳደር ቆይቷል፡፡
በ2001 ዓ.ም የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ማቋቋሚያ አዋጅም 587/2000 ተጠሪነቱም ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ነበረ፡፡ ከ2011 ዓ.ም የኩምሩክ ኮሚሺን በሚል ስያሚ ለገቢዎች ሚኒስተር ተጠሪ ተቋም ሆኖ ተግባሩን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ከ2011 ዓ.ም በወጣዉ አዋጅ አወጅ ቁጥር 1097/2011 እራሱን ችሎ የተቋቋመ ሲሆን ደንብ ቁጥር 437/2011 የኮሚሽኑ ስልጣንና ተግባር ተወስኖ ተቀምጧል፡፡
በ2014 ዓ.ም በሚኒስትሮች ም/ቤት በጣዉ የመንግሥት ተቋማት ማቋቋሚ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 በገቢዎች ሚኒስተር ተጠሪ ተቋም ሆኖ እንዲቀጥል ወስኑአል፡፡
ዕሴቶች
- አገልጋይነት
- ሙያዊ ብቃት
- በቡድን መሥራት
- መሰጠት
- ታማኝነት