ባለፉት ስምንት ቀናት የኮንትሮባንድ እቃዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 14 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ባለፉት ስምንት ቀናት የኮንትሮባንድ እቃዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 14 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
*************************************************************************
የጉምሩክ ኮሚሽን ከሐምሌ 21 ቀን እስከ 28 2014 ዓ.ም ባደረገው ዘመቻ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 14 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
ኮሚሽኑ በተጠቀሱት ቀናት 118 ነጥብ 5 ሚሊዮን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ የወጭ ፤ በድምሩ 127 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አቃቂ ቃሊቲ ፣ አዲስ አበባ ኤርፖርት ፣ እና ምያሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 25 ነጥብ 2 ሚሊዮን ፣ 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን እና 15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ናቸው።
የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡
የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaCustomsCommission