ደረሠኝ በዕቃ ወይም በአገልግሎት ግብይት ላይ ተመስርቶ ከሻጩ/አቅራቢው/ ለገዥው የሚሠጥና ግብይት ስለመፈፀሙ ፣ ገንዘብ ስለመሰብሰቡ ፣ ዋጋው ስለመከፈሉ ወይም ለወደፊት ለመክፈል ውል መግባቱን የሚያሣይ ሰነድ ነው፡፡ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 መሰረት ከደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች በስተቀር የደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋዮች የሒሳብ መዝገብ፣ አስፈላጊ መረጃዎችንና ደረሰኞችን የመያዝ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች የሒሳብ መዝገብ እንዲይዙ በህግ ባይገደዱም በፍላጎታቸው መያዝ ይችላሉ፡፡ የደረጃ “ሀ” እና የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የንግድ ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት ግብይቱ በደረሰኝ እንዲደገፍ ያደርጋሉ፡፡ለህጋዊ የንግድና የታክስ ስርዓት መጎልበት የሁሉም ዜጋ አስተዋጽኦ እንደተጠበቀ ሆኖ፤በሽያጭ ወቅት ደረሰኝ መስጠት የሻጭ፣መቀበል ደግሞ የገዥ ሃላፊነት ነዉ፡፡ለዛሬም አንድ ደረሰኝ መያዝ ስለሚገባዉ ዝርዝር መረጃ እና ደረሰኝ ተጠቃሚ ግብር ከፋይ ምን ምን ሃላፊነቶች እንዳሉበት መረጃዎችን እናደርሳለን፡፡

Today 20 Yesterday 18 Week 20 Month 198 All 8529

Currently are 29 guests and no members online