የሥጋት ሥራ አመራር

የስጋት ስራ አመራር ምን ማለት ነው?

የሥጋት ሥራ አመራር ማለት በጉምሩክ የሚስተናገዱ እቃዎች ላይ አገልግሎት አሰጣጡንና የቁጥጥር ሥርዓቱን ሚዛናዊ ባደረገ ሁኔታ በሚቀመጡ መስፈርቶች መሠረት የተለያየ የሥጋት ደረጃ በማውጣት የሚከናወን የአሠራር ሥርዓት ነው፤

የስጋት ደረጃ ዓይነቶች
የገቢና ወጪ ዕቃዎች በሚከተሉት የስጋት ደረጃ ተመድበዉ የጉምሩክ ስነ ሥርዓት ይፈጸምባቸዋል፡፡ እነዚህም፡-

• ሰማያዊ
• አርንጓዴ(ዝቅተኛ)
• ቢጫ(መካከለኛ)
• ቀይ(ከፍተኛ)

ቀይ ወይም ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ማለት ለገቢ ወይም ወጪ ዕቃዎች አካላዊ የዕቃ ፍተሸ እና የሰነድ ምርመራ ተደርጎ የሚለቀቁ ዕቃዎች ናቸው፡፡
ቢጫ ወይም መካከለኛ የስጋት ደረጃ ማለት ለገቢና ለወጪ ዕቃዎች ሰነድ ምርመራ ብቻ ተደርጎ የሚለቀቁ ዕቃዎች ናቸው፡፡
አረንጓዴ ወይም ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ማለት በመድረሻ ወይም በመነሻ ጣቢያ የደረሱ ዕቃዎች የሰነድ ምርመራ እና አካላዊ ፍተሸ ሳይደረግባቸው
የገቢ ወይም የወጪ ዕቃ ሰነድ እንደቀረበ በመልቀቅ በድህረ ዕቃ አወጣጥ ኦዲት ወይም /እና በሌሎች የህግ ማስከበር የስራ ክፍሎች ዕቃው ከተለቀቀ በኋላ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ናቸው፡፡
ሰማያዊ የስጋት ደረጃ ማለት የተመረጡ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ድርጅቶች (AEO) የሚስተናገዱበት የስጋት ደረጃ ሲሆን የሰነድ ምርመራ ወይም አካላዊ ፍተሸ ሳይደረግባቸው
ሰነድ እንደቀረበ ተለቀው በድህረ ዕቃ አወጣጥ ኦዲት ወይም/ እና በሌሎች የህግ ማስከበር የስራ ክፍሎች ዕቃው ከተለቀቀ በኋላ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ናቸው፡፡

Today 18 Yesterday 7 Week 25 Month 376 All 10738

Currently are 14 guests and no members online