ኤክሳይዝ ታክስ የቅንጦት እቃዎች ሆነው ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረም መሰረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ፣ እንዲሁም የሕብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱና ማህበራዊ ችግር የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃ በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ኤክሳይዝ ታክስ የተጀመረው በእንግሊዝ ፓርላማ በ1643 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱ የመንግስት ገቢን ከፍ ለማድረግ ታስቦ የተጣለ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ በኢትዮጵያም ታክሱ ከረጅም ጊዜያት ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን የመንግስትን የገቢ አቅም በማሳደጉ ረገድ የበኩሉን ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ ኤክሳይዝ ታክስ የቅንጦት እቃዎች ሆነው ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረም መሰረታዊ በመሆናቸው የገበያ ፍላጎታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ እንዲሁም የሕብረተሰቡን ጤንነት በሚጎዱና ማህበራዊ ችግር የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል የተጣለ ታክስ ነው፡፡ ታክሱ በአንዳንድ የተመረጡ ዕቃዎች ላይ ማለትም በሀገር ውስጥ በሚመረቱና ወደ አገር ውስጥ በሚገቡት ላይ ብቻ የሚጣል ነው፡፡ ኤክሳይዝ ታክስ አላማው ማህበራዊ ጠቀሜታ የሌላቸውን እና የህብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱ ምርቶችን መቀነስ፣ የቅንጦት የሆኑ የፍጆታ እቃዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደር እና የመንግስትን ገቢ ማሳደግ ናቸው፡፡ የመንግስትን ገቢ ማሳደግ ሲባል የተሻለ ገቢ ያላቸው ሠዎች በሚጠቀሙባቸው እቃዎች እና የመግዛት ፍላጎታቸው በማይቀንስባቸው ምርቶች ላይ ታክሱን በመጣል ለአገር ተጨማሪ ገቢ ማስገኘት ነው፡፡ የቅንጦት እቃዎች ከሠው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎት በላይ የሆኑ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ውድ የሆኑ መጠጦች፣ ሲጋራ፣ ሽቶና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡ ይህ የታክስ ዓይነት ለህብረተሰቡ ጤንነት አደጋ የሆኑ የትምባሆ እና ሌሎች ምርቶች ላይ ዋጋቸው እንዲጨምርና የተጠቃሚዎቹ ቁጥር እንዲቀንስ ታስቦ የሚጣልም ነው፡፡ በተጨማሪም የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታት እንዲሁም ከውጪ የሚገቡ እቃዎች ሀገር ውስጥ የተመረቱትን ከገበያ ውጭ እንዳያደርጓቸው ታስቦ ይጣላል። ይህ ታክስ ከሚጣልባቸው እቃዎች ውስጥ አንዱ መኪና ነው፡፡ የግል አውቶሞቢል ላይ አምስት ዓይነት ቀረጥና ታክስ ይጣላል፡፡ እነሱም፡- የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ሱር ታክስ እና ዊዝሆልዲንግ ታክስ ናቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት አምስቱ ታክሶች እያንዳንዳቸው የየራሳቸው የታክስ መጣኔ (tax rate) ያላቸው ሲሆን መጣኔዎቹ ከዚህ በታች በቀረበው ሠንጠረዥ ተመልክተዋል፡፡

ተ.ቁ የቀረጥና ታክስ ዓይነቶች መጣኔ በመቶኛ
1 የጉምሩክ ቀረጥ 35
2 ኤክሳይዝ ታክስ- የተሽከርካሪው ሲሊንደር አቅም (cyliderical capacity) እስከ 1300 ከሆነ 30
የተሽከርካሪው ሲሊንደር አቅም ከ1301 እስከ 1800 60
የተሽከርካሪው ሲሊንደር አቅም ከ1800 በላይ ከሆነ 100
3 ተጨማሪ እሴት ታክስ 15
4 ሱር ታክስ 10
5 ዊዝሆልዲንግ ታክስ 3
ለአዲስ የግል አውቶሞቢል የሚከፈለው ቀረጥና ታክስ የሚሰላው በአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ( Duty paying value) ላይ ተመርኩዞ ነው፡፡ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ለግል አውቶሞቢል የወጣው ወጪ ድምር ነው፡፡ ይህ ድምር አውቶሞቢል ለመግዛት (cost)፣ ለኢንሹራንስ (insurance)፣ እና ለማጓጓዝ (freight) እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ድረስ የወጣውን ወጪ ያካትታል፡፡ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ወደ ሀገራችን የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ የሚያሳይ መረጃ (data) ያጠናቀረ ሲሆን አስመጪው የቀረበውን ወጪ ከዚሁ የመረጃ ቋት ጋር በማመሳከር በሚገኘው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ መሰረት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሰላል፡፡ ለምሳሌ፡- የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 70,000፣ የሲሊንደር አቅሙ 1280 የሆነ አዲስ ቶዮታ ኮሮላ አውቶሞቢል ቢገባ፤ ቀረጥና ታክሱን ለመወሰን የሚከተሉት አምስት የስሌት ደረጃዎች ይሰላሉ፡፡ የመጀመሪያው የጉምሩክ ቀረጥ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ መጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 70,000 X 35/100 = 24,500 ይሆናል፡፡ በቀጣይ የሚሰላው ኤክሳይዝ ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይዝ ታክስ መጠን (70,000 + 24,500) x 30% = 28,350 ይሆናል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስ በመደመር በተጨማሪ እሴት ታክስ ሬት ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ ብር (70,000 + 24,500 + 28,350) X 15% = 18,427.5 ይሆናል፡፡ በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350+ 18,427.5) X 10% = 14,127.75 ብር ይሆናል፡፡ በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 70000 x 3/100 = 2100.00 ብር ይሆናል፡፡ በመጨረሻው የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክሶች ይደመራሉ፣ በዚህ መሰረት መንግስት ከአውቶሞቢሉ የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት ድምር 24,500 + 28,350+ 18,427.5 + 14,127.75 + 21,000 = 87505.25 ብር ይሆናል:: በራሄል ወልዴ

ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባቀረጥና ታክስ የሚታሰበው የተሸከርካሪዉን ሲሲ መሰረት በማድረግ CIF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡ ተሽከርካሪው ያገለገለ ከሆነ ከተመረተበት አንድ ዓመት ጊዜ ጀምሮ ከFOB ዋጋዉ ላይ በየዓመቱ 10% በመቀነስ በጠቅላላዉ እስከ 3 አመት ወይም 30% ድረስ የእርጅና ቅናሽ ካለዉ በማስላት የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ በማባዛት ቀረጥና ታክሱን ማወቅ ይቻላል፡፡ የተሽከርካሪው የፈረስ ጉልበት ማለትም ሲሲው 1300 ከሆነ 125%ሲሆን 1301ሲሲ እስከ 2500 ሲሲ ደግሞ ከ176.24% እስከ 244.55% ባሉትየጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ ይሰላል፡፡ለሰው ማጓጓዣ የሚያገለግሉ ሌሎች ተሸከርካሪዎች ሲሆን ደግሞ በሌላ ስፍራ ያልተጠቀሰ ከሆነ የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔ 125.00075% ሲሆን ሹፌሩን ጨምሮ አስር ወይም ከዛ በላይ ሰዎችን ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ ተሸከርካሪዎች ከ15 ተጓዦች ያነሰ መቀመጫ ያላቸው ተሸከርካሪዎች 58.25% እንዲሁም 15 እና ከዚያ በላይ ሰው የሚይዝ መቀመጫ ያላቸው የጉምሩክና ሌሎች ቀረጦች ጠቅላላ ምጣኔው 29.50% ነው፡፡ የተሽከርካሪው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡ የተሸከርካሪ ቀረጥና ታክስ ለመወሰን አምስት የሰሌት ደረጃዎችን(ማለትም የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይስ ታክስ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣ ሱር ታክስ እና ዊዝሆልዲንግ ታክስ) እንከተላለን፡፡ የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት እንደሚታሰብ በምሳሌ እንመልከት፡፡ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 70000፣ የሲሊንደር አቅሙ 1280 የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ሲገባ:- በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 70,000 X 35% =24,500 ይሆናል፡፡ ቀጥሎ ኤክሳይስ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (70,000 + 24,500) 30%=28,350 ይሆናል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350) 15% = 18,427.5 ብር ይሆናል፡፡ በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (70,000 + 24,500 + 28,350 +18,427.5)10%= 14,127.75 ብር ይሆናል፡፡ በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 70,000 X 3%= 2,100 ብር ይሆናል፡፡ በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት 24,500 + 28,350 + 18,427.5 + 14,127.75 + 2,100= 87,505.25 ብር ይሆናል፡፡

car

Debela

የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ መመሪያ ተሻሻለ (መጋቢት 23/2011 ዓ.ም) ከዚህ ቀደም በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ አፈፃፀምን በተመለከተ አገልግሎት ላይ የነበሩትን 4 ሰርኩላሮችንና 6 መመሪያዎችን በአንድ በማካተት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ መመሪያ ቁጥር 148/2011 ሆኖ ፀድቋል፡፡ በዚህ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 15/1996፣ቅይጥ አቅርቦት እንዲሁም የካፒታል ግንባታ ሲከናወን የተከፈለን የተጨማሪ እሴት ታክስ ስለማቀናነስ የወጣ መመሪያ ቁጥር 20/2001፣ ለሰብዓዊ እርዳታ ስለሚውል እቃዎች እና አገልግሎቶች የታክስ ነፃ መብት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 23/2001 እና ለባለ ልዩ መብት ድርጅቶች ስራ ማስፈፀሚያ እንዲውል በሚከናወን የዕቃ እና የአገልግሎት ግዢ ላይ የተከፈለ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚደረግበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 24/2000 ተሽረዋል፡፡ መመሪያውን ማሻሻል ያስፈለገበት ምክኒያትም ከዚህ ቀደም በተበታተነ ሁኔታ በመውጣታቸው የተንዛዙና ለመረዳት አስቸጋሪ የነበሩ መመሪያዎችንና ሰርኩላሮችን ወደ አንድ በማሰባሰብ ለግብር ከፍዩ ምቹና ቀልጣፍ አገልግትን ለመስጠት ታስቦ ነው፡፡ ይህ መመሪያ ተግባራዊ ሲደረግም የተመላሽ አገልግሎት ለመስጠት ይወስድ የነበረውን 60 ቀን ወደ 45 ቀን የሚቀንስ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የደረሰኝ ህትመት ፈቃድ አሰጣጥ ፣አያያዝ ፣አጠቃቀም፣ አወጋገድ እና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 110/2008 ተሽሮ የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 149/2011 ፀድቋል፡፡

ደረሠኝ በዕቃ ወይም በአገልግሎት ግብይት ላይ ተመስርቶ ከሻጩ/አቅራቢው/ ለገዥው የሚሠጥና ግብይት ስለመፈፀሙ ፣ ገንዘብ ስለመሰብሰቡ ፣ ዋጋው ስለመከፈሉ ወይም ለወደፊት ለመክፈል ውል መግባቱን የሚያሣይ ሰነድ ነው፡፡ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 መሰረት ከደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች በስተቀር የደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋዮች የሒሳብ መዝገብ፣ አስፈላጊ መረጃዎችንና ደረሰኞችን የመያዝ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች የሒሳብ መዝገብ እንዲይዙ በህግ ባይገደዱም በፍላጎታቸው መያዝ ይችላሉ፡፡ የደረጃ “ሀ” እና የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የንግድ ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት ግብይቱ በደረሰኝ እንዲደገፍ ያደርጋሉ፡፡ለህጋዊ የንግድና የታክስ ስርዓት መጎልበት የሁሉም ዜጋ አስተዋጽኦ እንደተጠበቀ ሆኖ፤በሽያጭ ወቅት ደረሰኝ መስጠት የሻጭ፣መቀበል ደግሞ የገዥ ሃላፊነት ነዉ፡፡ለዛሬም አንድ ደረሰኝ መያዝ ስለሚገባዉ ዝርዝር መረጃ እና ደረሰኝ ተጠቃሚ ግብር ከፋይ ምን ምን ሃላፊነቶች እንዳሉበት መረጃዎችን እናደርሳለን፡፡

Page 2 of 2

Today 0 Yesterday 21 Week 21 Month 199 All 8530

Currently are 39 guests and no members online