ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የወጭና የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡
ኮሚሽኑ ህገወጥነትን ለመከላከል ባደረገው ዘመቻም ሀገር ልታጣ የነበረውን ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን ተችሏል

**********************************************************************
በያዝነው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የወጭና የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዙ ሲሆን
ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገንዘብ ሲተመን በ854 ሚሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሀዋሳ ፣ ጅግጅጋ እና ድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ
በቅደም ተከተላቸው 372፣ 320 እና 263 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድን ፍሰት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃን የሚይዙት ተሸከርካሪዎች፣ አዳዲስ አልባሳትና ኤሌክትሮኒክሶች ናቸው፡፡ የገቢ ኮንትሮባንድ አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋቸውም ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ነው፡፡

ሞያሌ፣ አዲስ አበባ ኤርፖርትና ሀዋሳ ከፍተኛ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዘባቸው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በዓይነት ሲገለጹም
አደንዛዥ እጾች 51 በመቶ ( 260 ሚሊዮን ብር )፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር 23 በመቶ (116 ሚሊዮን ብር ) እና ማእድናት 12 በመቶ በገንዝብ ሲተመን 61 ሚሊዮን ብር በላይ ይሸፍናሉ፡፡
ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ ሀገራት ሊተላለፉ ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ የኮንትሮባንድ እቃዎች አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋቸውም
ከ502 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል
ጉምሩክ ኮሚሽን የተለያዩ ስልቶችን በመንደፍ ከፌደራል ፖሊስና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡

ኮሚሽኑ በተጠቀሰው የጊዜ ማእቀፍ ውስጥም ባከናወናቸው በኢንተለጀንስ ስራዎች፣ በድንገተኛ ፍተሻዎች ፣ የገቢና ወጭ ኮንትሮባንድ
ክትትልና በሌሎች ተግባራት መንግስት ሊያጣው የነበረውን ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን ተችሏል፡፡
ሶስት አመታትን ሊደፍን ጥቂት ወራት የቀሩት ሀገራዊ ለውጥ እንዲመጣ ካስቻሉት ዓበይት ምክንያቶች አንዱ የህገወጥነት መስፋፋት ነው፡፡ ከእነዚህ ህገወጥ ተግባራት መካከል ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ መንግስት የችግሩን አሳሳቢነት ለመቅረፍ በተለይም ከለውጡ በኋላ በርካታ አመርቂ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ነገር ግን ከችግሩ ስፋትና ተለዋዋጭነት አንጻር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እና እድገት እንዲቀጭጭ፣ የንግድ ስርዓታችን እንዲዛባ፣ሀገር ደህንነት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ የዜጎች ጤናም አደጋ ላይ እንዲወድቅ የሚያደርግ ውስብስብ ችግር ነው፡፡ ይህን አደጋ በሚገባ ካልመከትነው ልንቆጣጠረው ወደማንችለው ቀውስና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ውስጥ ሊያስገባን ስለሚችል በጋራ ልንመክተው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን ለመከላከል ያለመ የንቅናቄ መድረክ በአዳማ ከተማ ሲካሔድ ከተናገሩት የተወሰደ
< የኮሚሽኑ የኢንተለጀንስና ኮንትሮባንድ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተገኔ ደረሰ በያዝነው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና ኬላዎች ከ1.3 በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ከገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች መካካል ተሽከርካሪዎች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ አደንዛዥ እጽ፣ ማእድናት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በቅደም ተከተል በውጭ ኮንትሮባንድ የተያዙና ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙ እቃዎች መሆናቸውን አቶ ተገኔ አስረድተዋል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የወጭና የገቢ ንግድ ጤናማ እንዲሆንና ተጨባጭ የሆኑ ለውጦች እንዲመጡ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን የገለጹት አቶ ተገኔ በዚህም በ2013 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ ከ55 ቢሊዮን በላይ ብር ገቢ ተሰብስቧል፡፡ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2.9 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ የኮንትሮባንድ ግብረኃይል እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በተሟላ መልኩ አለመደራጀት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቂ አለመሆን፣ አንዳንድ የጸጥታ አባላትና አመራሮች ተባባሪ አለመሆን እና ሌሎች ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመከላከል ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮች መሆናቸውን አቶ ተገኔ አስገንዝበዋል፡፡ ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን ለመከላከል ያለመ የንቅናቄ መድረክ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር የህግ ተገዥነት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ፣ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ አባገዳዎች የኃይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡
ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቋማት የተቀናጀ ስራ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ ከጊዜ ወደ ጊዜ በዓይነቱና በአፈጻጸም ስልቱ መልኩን እየቀያየረ የመጣውን ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ስራ መስራት ይገባቸዋል ሲሉ በጸረ ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ መከላከል የንቅናቄ መድረክ የተሳተፉ አካላት ገልጸዋል፡፡ በአዳማ ከተማ በዛሬው እለት በተጀመረው በዚህ የንቅናቄ መድረክ ከኦሮሚያ ክልል ከሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የጸጥታ አካላት፣ ዐቃብያነ ሕግ፣ ዳኞች ፣ የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉት ስራዎች አበረታች ቢሆኑም ከችግሩ አሳሳቢነትና ስፋት አንጻር የሚመለከታቸው ተቋማት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን ኢንተለጀንሲ ኮንትሮባንድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተገኔ ደረሰ እንደገለጹት ኮሚሽኑ ብቻውን ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድና ለመከላከልና ለመቆጣጠር ስለማይችልና የብዙ ተቋማትን ሚና ስለሚጠይቅ የሚመለከታቸው አካላት ተቀናጅተውና ተናበው በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው አስረድተዋል፡፡ በጉምሩክ ህግ ዙሪያ የመወያያ ጹሁፍ ያቀረቡት የፍትሐቤር ቡድን አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ጥላሁን ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ አሁን ካለበት አሳሳቢ ደረጃ ለመቀነስና በሀገር ላይ የሚያመጣው ዘርፈ ብዙ አደጋ ለመከላከል ጠንካራ የመረጃ ለውውጥና አፋጣኝ የሆነ የፍትህ አሰጣጥ ሊኖር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ የሀገር ኢኮኖሚ እንዲቀጭጭ ከሚያሳድረው ተጽእኖ በተጨማሪ በዜጎች ጤንነት ላይ እንዲሁም በሀገር ደህንነት የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት አቶ ሀብታሙ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት እያንዳንዱ ተቋም የሚጠበቅበትን የተናጠልና የጋራ ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ የታክስ ወንጀሎችን ለመከላከል የጸጥታ አካላት ሚናን በተመለከተ ጹሑፍ ያቀረቡት በገቢዎች ሚኒስቴር የታከስ ማጭበርበርና ምርመራ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገዙ ለታክስ አስተዳደሩ ተግዳሮት በሆኑት ታክስ ማጭበርበርና ስወራ ላይ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን የፍትሕ አካላት ታክስ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ልዩ ትኩረት በመስጠትና ህግን በማስከበር ስራው አጋር እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡ በህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች የፍትህ አሰጣጥ መጓተት፣ የማስረጃ እጥረት፣ የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አለመወጣት እና የአገልግሎት አሰጣጥ በሚጠበቀው ደረጃ አለመዘመን ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን ለመከላከል ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸው በመደረኩ የተነሱ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተሰነዘሩትን አስተያየቶችና ጥያቄዎች በሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡

ከ250 ሺ ዶላር በላይ የሚያወጡ የኮቪድ 19 መከላከያ ግብአቶች ለኮሚሽኑ ድጋፍ ተደረገ::

ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የተባለ ድርጅት የኮሮና ወረርሽ መከላከያ የሚሆኑና ከ250 ሺ ዶላር በላይ የሚያወጡ ግብአቶችን ለጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ ጥር 29/2013 ዓ.ም አበርክቷል፡፡ የድጋፍ ርክክቡ በኮሚሽኑ ዋና መስሪያቤት ሲደረግ የተገኙት የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ በየነ የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በሀገራችን በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖዎችን እያሳደረ እንደሚገኝ ገልጸው በሽታውን ለመከላከልም መደጋገፍና መተባበር አስፈላጊ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የተደረገው የኮቪድ 19 መከላከያ ግብአቶች ድጋፍ የዚሁ ትብብር ማሳያና ተምሳሌት እንደሆነ ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቅሰው ተጋላጭ ለሆኑና በተለያዩ የሀገራችን መግቢያዎች ለሚገኙ የኮሚሽኑ ሰራተኞች በአጭር ጊዜ እንደሚከፋፈልም ጠቅሰዋል፡፡ የትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ አቶ ታደሰ ተፈራ በበኩላቸው ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የህብረተሰቡን ሕይወት የሚቀይሩ የተለያዩ የልማትን ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተው ከመደበኛ ስራዎቹ በተጨማሪ በሀገራችን የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ርብርብ የራሱን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የሀገራችን ኢኮኖሚ እንዲያድግና የንግዱ ክፍለኢኮኖሚም እንዲዘምን ከሚያደርጉ ወሳኝ ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ታደሰ የድጋፉ ዓላማም በወረርሽኑ ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ የኮሚሽኑ ሰራተኞችን ለመታደግና የኮሚሽኑ መደበኛ ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ ለማድረግ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

Page 1 of 2

Today 18 Yesterday 7 Week 25 Month 376 All 10738

Currently are 11 guests and no members online