k

ለሶስት ዓመታት የተጠራቀሙ ውዝፍ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነዉ (መጋቢት 19/2011 ዓ.ም) በሲስተም እና ኔትወርክ መቆራረጥ ምክንያት ለሶስት ዓመታት የተጠራቀሙ የታክስ መረጃ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ እንደሆነ የታክስ መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ት ራቢያ ይማም ገለጹ፡፡ ዳይሬክተሯ እንዳሉት ላለፉት ሶስት ዓመታት በአገራችን በነበረዉ በሲስተም እና ኔትወርክ መቆራረጥ ችግር ምክንያት በተለይ በዋናዉ መስሪያ ቤት የመረጃ አሰባሰቡ ስራ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ያህል በአገሪቱ በነበሩ ችግሮች ተቋርጦ ስለነበር ውዝፍ ስራ እዲኖር ያደረገ ሲሆን ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ጋር በተገናኘ የተሰበሰቡ እና የሚወገዱ መሳሪያዎች እንዲሁም ፊዚካል ሚሞሪዎች መረጃ ለማጣራት የተሰራው ስራ አመርቂ ነው፡፡ የ202 ሺ ድርጅቶች ውዝፍ መረጃ የነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ 70 ሺ የሚሆኑትን መረጃዎች ወደሲስተም ማስገባት ተችሏል፡፡ ሙሉ በሙሉ የተወገዱ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች አደራጅተው ተጠቃሚው በሚፈልገው ሰዓት አንስቶ ለመስጠት በሚያስችል ደረጃ ተደራጅቶ ተቀምጧል፡፡ በተጨማሪም የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን ብቻ ሳይሆን ማንዋል ደረሰኞችንም ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

Today 1 Yesterday 21 Week 22 Month 200 All 8531

Currently are 39 guests and no members online