ከ250 ሺ ዶላር በላይ የሚያወጡ የኮቪድ 19 መከላከያ ግብአቶች ለኮሚሽኑ ድጋፍ ተደረገ::

ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የተባለ ድርጅት የኮሮና ወረርሽ መከላከያ የሚሆኑና ከ250 ሺ ዶላር በላይ የሚያወጡ ግብአቶችን ለጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ ጥር 29/2013 ዓ.ም አበርክቷል፡፡ የድጋፍ ርክክቡ በኮሚሽኑ ዋና መስሪያቤት ሲደረግ የተገኙት የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ በየነ የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በሀገራችን በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖዎችን እያሳደረ እንደሚገኝ ገልጸው በሽታውን ለመከላከልም መደጋገፍና መተባበር አስፈላጊ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የተደረገው የኮቪድ 19 መከላከያ ግብአቶች ድጋፍ የዚሁ ትብብር ማሳያና ተምሳሌት እንደሆነ ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቅሰው ተጋላጭ ለሆኑና በተለያዩ የሀገራችን መግቢያዎች ለሚገኙ የኮሚሽኑ ሰራተኞች በአጭር ጊዜ እንደሚከፋፈልም ጠቅሰዋል፡፡ የትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ አቶ ታደሰ ተፈራ በበኩላቸው ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የህብረተሰቡን ሕይወት የሚቀይሩ የተለያዩ የልማትን ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተው ከመደበኛ ስራዎቹ በተጨማሪ በሀገራችን የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ርብርብ የራሱን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የሀገራችን ኢኮኖሚ እንዲያድግና የንግዱ ክፍለኢኮኖሚም እንዲዘምን ከሚያደርጉ ወሳኝ ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ታደሰ የድጋፉ ዓላማም በወረርሽኑ ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ የኮሚሽኑ ሰራተኞችን ለመታደግና የኮሚሽኑ መደበኛ ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ ለማድረግ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

Today 1 Yesterday 21 Week 22 Month 200 All 8531

Currently are 30 guests and no members online