< የኮሚሽኑ የኢንተለጀንስና ኮንትሮባንድ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተገኔ ደረሰ በያዝነው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና ኬላዎች ከ1.3 በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ከገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች መካካል ተሽከርካሪዎች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ አደንዛዥ እጽ፣ ማእድናት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በቅደም ተከተል በውጭ ኮንትሮባንድ የተያዙና ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙ እቃዎች መሆናቸውን አቶ ተገኔ አስረድተዋል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የወጭና የገቢ ንግድ ጤናማ እንዲሆንና ተጨባጭ የሆኑ ለውጦች እንዲመጡ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን የገለጹት አቶ ተገኔ በዚህም በ2013 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ ከ55 ቢሊዮን በላይ ብር ገቢ ተሰብስቧል፡፡ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2.9 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ የኮንትሮባንድ ግብረኃይል እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በተሟላ መልኩ አለመደራጀት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቂ አለመሆን፣ አንዳንድ የጸጥታ አባላትና አመራሮች ተባባሪ አለመሆን እና ሌሎች ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመከላከል ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮች መሆናቸውን አቶ ተገኔ አስገንዝበዋል፡፡ ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን ለመከላከል ያለመ የንቅናቄ መድረክ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር የህግ ተገዥነት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ፣ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ አባገዳዎች የኃይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡

Today 1 Yesterday 21 Week 22 Month 200 All 8531

Currently are 29 guests and no members online