ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የወጭና የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡
ኮሚሽኑ ህገወጥነትን ለመከላከል ባደረገው ዘመቻም ሀገር ልታጣ የነበረውን ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን ተችሏል

**********************************************************************
በያዝነው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የወጭና የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዙ ሲሆን
ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገንዘብ ሲተመን በ854 ሚሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሀዋሳ ፣ ጅግጅጋ እና ድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ
በቅደም ተከተላቸው 372፣ 320 እና 263 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድን ፍሰት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃን የሚይዙት ተሸከርካሪዎች፣ አዳዲስ አልባሳትና ኤሌክትሮኒክሶች ናቸው፡፡ የገቢ ኮንትሮባንድ አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋቸውም ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ነው፡፡

ሞያሌ፣ አዲስ አበባ ኤርፖርትና ሀዋሳ ከፍተኛ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዘባቸው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በዓይነት ሲገለጹም
አደንዛዥ እጾች 51 በመቶ ( 260 ሚሊዮን ብር )፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር 23 በመቶ (116 ሚሊዮን ብር ) እና ማእድናት 12 በመቶ በገንዝብ ሲተመን 61 ሚሊዮን ብር በላይ ይሸፍናሉ፡፡
ከሀገር ውስጥ ወደ ውጭ ሀገራት ሊተላለፉ ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ የኮንትሮባንድ እቃዎች አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋቸውም
ከ502 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል
ጉምሩክ ኮሚሽን የተለያዩ ስልቶችን በመንደፍ ከፌደራል ፖሊስና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡

ኮሚሽኑ በተጠቀሰው የጊዜ ማእቀፍ ውስጥም ባከናወናቸው በኢንተለጀንስ ስራዎች፣ በድንገተኛ ፍተሻዎች ፣ የገቢና ወጭ ኮንትሮባንድ
ክትትልና በሌሎች ተግባራት መንግስት ሊያጣው የነበረውን ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን ተችሏል፡፡

Today 18 Yesterday 7 Week 25 Month 376 All 10738

Currently are 12 guests and no members online