በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ እና ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የወርቅ ጥፍጥፎች በቁጥጥር ስር ዋሉ:: በወቅታዊው የገበያ ዋጋ 12 ሚሊዮን 350 ሺህ ብር የሚያወጡ እና በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ አምስት የወርቅ ጥፍጥፎች በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ የወርቅ ጥፍጥፎቹ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ማእከል (NISS) በሰጠው ጥቆማ መሰረት የተገኘኙ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ ላይም የፌደራል ፖሊስ ምርምራ እያደረገ ይገኛል። ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እና የሚወጡ የኮንትሮባድ እቃዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሁሉም ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ሲሆን ለዚህ ስራ ስኬታማነት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ማእከል፣ የፌደራል ፖሊስ ኤርፖርት ዲቪዥን እና የአየር መንገድ ደህንነት መስሪያ ቤት ያበረከቱት አስተዋጥኦ ከፍተኛ ነው ፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል የጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን የስተላልፋል::

Today 5 Yesterday 6 Week 51 Month 260 All 11841

Currently are 15 guests and no members online