< የኮሚሽኑ የኢንተለጀንስና ኮንትሮባንድ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተገኔ ደረሰ በያዝነው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና ኬላዎች ከ1.3 በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ከገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች መካካል ተሽከርካሪዎች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ አደንዛዥ እጽ፣ ማእድናት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በቅደም ተከተል በውጭ ኮንትሮባንድ የተያዙና ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙ እቃዎች መሆናቸውን አቶ ተገኔ አስረድተዋል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የወጭና የገቢ ንግድ ጤናማ እንዲሆንና ተጨባጭ የሆኑ ለውጦች እንዲመጡ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን የገለጹት አቶ ተገኔ በዚህም በ2013 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ ከ55 ቢሊዮን በላይ ብር ገቢ ተሰብስቧል፡፡ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2.9 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ የኮንትሮባንድ ግብረኃይል እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በተሟላ መልኩ አለመደራጀት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቂ አለመሆን፣ አንዳንድ የጸጥታ አባላትና አመራሮች ተባባሪ አለመሆን እና ሌሎች ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመከላከል ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮች መሆናቸውን አቶ ተገኔ አስገንዝበዋል፡፡ ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን ለመከላከል ያለመ የንቅናቄ መድረክ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር የህግ ተገዥነት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ፣ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ አባገዳዎች የኃይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡

ከ250 ሺ ዶላር በላይ የሚያወጡ የኮቪድ 19 መከላከያ ግብአቶች ለኮሚሽኑ ድጋፍ ተደረገ::

ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የተባለ ድርጅት የኮሮና ወረርሽ መከላከያ የሚሆኑና ከ250 ሺ ዶላር በላይ የሚያወጡ ግብአቶችን ለጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ ጥር 29/2013 ዓ.ም አበርክቷል፡፡ የድጋፍ ርክክቡ በኮሚሽኑ ዋና መስሪያቤት ሲደረግ የተገኙት የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ በየነ የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በሀገራችን በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖዎችን እያሳደረ እንደሚገኝ ገልጸው በሽታውን ለመከላከልም መደጋገፍና መተባበር አስፈላጊ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የተደረገው የኮቪድ 19 መከላከያ ግብአቶች ድጋፍ የዚሁ ትብብር ማሳያና ተምሳሌት እንደሆነ ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቅሰው ተጋላጭ ለሆኑና በተለያዩ የሀገራችን መግቢያዎች ለሚገኙ የኮሚሽኑ ሰራተኞች በአጭር ጊዜ እንደሚከፋፈልም ጠቅሰዋል፡፡ የትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ አቶ ታደሰ ተፈራ በበኩላቸው ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የህብረተሰቡን ሕይወት የሚቀይሩ የተለያዩ የልማትን ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተው ከመደበኛ ስራዎቹ በተጨማሪ በሀገራችን የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ርብርብ የራሱን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን የሀገራችን ኢኮኖሚ እንዲያድግና የንግዱ ክፍለኢኮኖሚም እንዲዘምን ከሚያደርጉ ወሳኝ ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ታደሰ የድጋፉ ዓላማም በወረርሽኑ ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ የኮሚሽኑ ሰራተኞችን ለመታደግና የኮሚሽኑ መደበኛ ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ ለማድረግ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

weapon

ብዛቱ 980 የሆነ የክላሽ ጥይት በህገ ወጥ መንግድ ሲጓጓዝ አዋሽ ኬላ ላይ ተያዘ መጋቢት 20/2011 ዓ.ም ዛሬ ጠዋት ከሃረር ወደ አዳማ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-60292 ኦሮ በሆነ ተሽከርካሪ ላይ አዋሽ ጉምሩክ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ 980 የክላሽ ጥይት ተይዟል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የመኪናዉ ሹፌርና ረዳት ጨምሮ ከእቃዉ ጋር ግንኙነት ይኖረዋል ተብሎ የተጠረጠረ ዋና ሳጂን አሮጌ ገሪሶ የተባለዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዉሎ ጉዳዩ እየተጣራ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ ዜና ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በሃዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን በአለታ ወንዶ አከባቢ በአዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞችና በፌደራል ፖሊስ አባላት አማካኝነት በተከማቸበት መጋዘን መጋቢት 16/2011 በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡ በዚህ መሰረት የምግብ ዘይት 6960 ሊትር ግምታዊ ዋጋዉ 194 880 ስኳር 45 ኩንታል ግምታዊ ዋጋዉ 108000 ብር 30 ኩንታል ቡና ግምታዊ ዋጋዉ 300000 ብር እና ልባሽ ጨርቅ 5170 ኪሎ ግራም ግምታዊ ዋጋዉ 129250 ብር የሆነ ተይዟል፡፡

k

ለሶስት ዓመታት የተጠራቀሙ ውዝፍ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነዉ (መጋቢት 19/2011 ዓ.ም) በሲስተም እና ኔትወርክ መቆራረጥ ምክንያት ለሶስት ዓመታት የተጠራቀሙ የታክስ መረጃ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ እንደሆነ የታክስ መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ት ራቢያ ይማም ገለጹ፡፡ ዳይሬክተሯ እንዳሉት ላለፉት ሶስት ዓመታት በአገራችን በነበረዉ በሲስተም እና ኔትወርክ መቆራረጥ ችግር ምክንያት በተለይ በዋናዉ መስሪያ ቤት የመረጃ አሰባሰቡ ስራ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ያህል በአገሪቱ በነበሩ ችግሮች ተቋርጦ ስለነበር ውዝፍ ስራ እዲኖር ያደረገ ሲሆን ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ጋር በተገናኘ የተሰበሰቡ እና የሚወገዱ መሳሪያዎች እንዲሁም ፊዚካል ሚሞሪዎች መረጃ ለማጣራት የተሰራው ስራ አመርቂ ነው፡፡ የ202 ሺ ድርጅቶች ውዝፍ መረጃ የነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ 70 ሺ የሚሆኑትን መረጃዎች ወደሲስተም ማስገባት ተችሏል፡፡ ሙሉ በሙሉ የተወገዱ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች አደራጅተው ተጠቃሚው በሚፈልገው ሰዓት አንስቶ ለመስጠት በሚያስችል ደረጃ ተደራጅቶ ተቀምጧል፡፡ በተጨማሪም የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን ብቻ ሳይሆን ማንዋል ደረሰኞችንም ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

7.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ የሆነ የብር ጌጣጌጥ በቁጥጥር ስር ዋለ (የገቢዎች ሚኒስቴር፣ መጋቢት 23/2011 ዓ.ም) በሞያሌ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ግምታዊ ዋጋው 7.5 ሚሊዮን ብር የሆነ በኮንትሮባንድ የገባ የጣሊያን ስሪት የብር ጌጣጌጥ መጋቢት 21 ቀን 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የብር ጌጣጌጡ 151 ኪ.ግ የሚመዝ ን ሲሆን ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል :: የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3አአ- 81376 በሆነ ተሸከርካሪ ሲጓጓዝ በነበረበት ወቅት ነው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡ኮንትሮባንድን የመከላከል ስራው ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

Page 1 of 2

Today 0 Yesterday 21 Week 21 Month 199 All 8530

Currently are 36 guests and no members online