ኮሚሽኑ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት 176 ሺህ መጻህፍትን አበረከተ

Resultados da pesquisa

Aplicações Aninhadas

Publicador de Conteúdos e Mídias

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Sex, 8 mar 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Ter, 27 fev 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Qua, 21 fev 2024

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡ Seg, 12 fev 2024

Publicador de Conteúdos e Mídias

Publicador de Conteúdos e Mídias

null ኮሚሽኑ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት 176 ሺህ መጻህፍትን አበረከተ

ኮሚሽኑ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት 176  ሺህ  መጻህፍትን አበረከተ
*****************************************
 “አንድ ሚሊዮን መጻህፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ“ በሚል መሪ ቃል አንድ ሚሊዮን መጻህፍት ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ለማሰባሰብ የተደረገውን ጥሪ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን   በዛሬው ዕለት የተለያዩ ይዘት ያላቸውን 176 ሺህ መጻህፍትን አስረክቧል።
በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ ፕሬዝደንት ክብርት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፤ የተማረ የተመራመረ ትውልድ ለመፍጠር የቤተመጻህፍት ሚና  አይተኬ መሆኑን ገልጸው፣ ይህንን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ሁሉም ዜጋ ለቤተመጻህፍቱ መጻህፍትን እንዲያበረክት ጠይቀዋል ። የጉምሩክ ኮሚሽን ላደረገው ድጋፍም ፕሬዝዳንቷ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወ/ሃና በበኩላቸው ፤ አብርሆት ቤተመፃህፍትን የተለየ እና የተደራጀ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ለአንድ ወር በሚቆየው በዚህ የመጻህፍት ማሰባሰብ መርሃ ግብርም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት እና መጻህፍቱን ያስረከቡት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ ”ይህንን ትልቅ ሃገራዊ ጥሪ ተቀብለን የዚህ ታሪክ ተካፋይ በመሆናችን ድርብ ክብር  ይሰማናል” ሲሉ ገልፀዋል።
ኮሚሽነር ደበሌ አክለውም፣ ኮሚሽኑ ከአሁን በፊት 1.4 ሚሊዮን መጻህፍትን ለአብርሆት ቤተመጻህፍት መለገሱን አስታውሰው መጻህፍት ትውልድን የሚገነቡ እና  የሚያንጹ በመሆናቸው ኮሚሽኑ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን  ለቤተመጻህፍቱ  ላደረገው ድጋፍም የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡

 

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Publicador de Conteúdos e Mídias

Aplicações Aninhadas

Publicador de Conteúdos e Mídias

ጠቃሚ መረጃዎች