የጉምሩክ ኮሚሽን በዘጠነኛው ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት መርሃ ግብር " የከፍተኛ አድናቆት የምስክር ወረቀት " ተበረከተለት።
የጉምሩክ ኮሚሽን በዘጠነኛው ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት መርሃ ግብር " የከፍተኛ አድናቆት የምስክር ወረቀት " ተበረከተለት።
***********************************
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዘጠነኛውን ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ በተገኙበት ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ. ም አካሂዷል፡፡
በሽልማቱም የተሳትፎ ፤ የአድናቆት እና የከፍተኛ አድናቆት የምስክር ወረቀቶች ፤ እንዲሁም የሶስተኛ እና የሁለተኛ ደረጃ የዋንጫ ሽልማቶችን መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ሰጥቷል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንም በዚህ የሽልማት መርሃ ግብር የከፍተኛ አድናቆት የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።
ይህ ውጤት በአመራሩ እና በሰራተኛው ከፍተኛ ርብርብ የተገኘ በመሆኑ የጉምሩክ ኮሚሽን እንደ ሁልጊዜው ምስጋናውን ያቀርባል ::
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
Facebook (https://www.facebook.com/ecczena)