ከ141 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Sökresultat

Kapslade applikationer

Innehållspublicerare

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ fr, 8 mar 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ti, 27 feb 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ on, 21 feb 2024

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡ må, 12 feb 2024

Innehållspublicerare

Innehållspublicerare

null ከ141 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከጥቅምት 25 ቀን እስከ ህዳር አንድ ባደረገው ክትትል 92 ነጥብ 6  ሚሊዮን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 49 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የወጭ  በድምሩ 140 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ  የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ  ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣  ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት   እና የተለያዩ  ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ጅግጅጋ፣ ድሬድዋ እና ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 21 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፣ 14  ሚሊዮን 95 ሺህ  ብር እና 14 ሚሊዮን 24 ሺህ ብር  በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ 25 ግለሰቦች እና ዘጠኝ ተሽከርካሪዎች  በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaCustomsCommission

 

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Innehållspublicerare

Kapslade applikationer

Innehållspublicerare

ጠቃሚ መረጃዎች