የኮንትሮባንድ ወንጀል የሃገር እና የህዝብ ሥጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ያለው ቅንጅታዊ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ

Search Results

Nested Applications

Asset Publisher

null የኮንትሮባንድ ወንጀል የሃገር እና የህዝብ ሥጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ያለው ቅንጅታዊ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ

የኮንትሮባንድ ወንጀል የሃገር እና የህዝብ ሥጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ያለው ቅንጅታዊ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ
***************************
የጉምሩክ ኮሚሽን በ2014 የበጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን  ጋር በመቀናጀት ኮንትሮባንድን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ የተሰሩ ሥራዎችን እና ያጋጠሙ ችግሮችን አስመልክቶ ከፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቢሾፍቱ ከተማ  ውይይት ተደርጓል።

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ የህግ ተገዢነት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ በየነ፤ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ የአፈፃፀም ስልቱ ተለዋዋጭ እና በታጠቁ ኃይሎች ጭምር የሚፈጸም በመሆኑ ለቁጥጥር አስቸጋሪ እንዳደረገው ገልፀዋል::

የኮንትሮባንድ ዝውውር ለህዝብ ጤንነት አስጊ ከሆኑ ቍሳቀሶች በተጨማሪ  ለሐገር ደህንነት እስከሆኑ የጦር መሳሪያዎች መድረሱን አቶ ሙሉጌታ ጠቁመው ድርጊቱን ለመከላከል ከፌደራል ፖሊስ ጋር ያለው ቅንጅታዊ  ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኮንትሮባንድ ዝውውርን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ የተሰሩ ሥራዎች በጉምሩክ ኮሚሽን  የኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ተገኔ ደረሰ የቀረቡ ሲሆን የተገኙ ሥኬቶች እና የታዩ ወሱኑነቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል ::

አቶ ተገኔ በሪፖርታቸው ፤የጉምሩክ ኮሚሽን  በዘንድሮው የበጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ባደረገው  ክትትል 398 ነጥብ 7  ሚሊዮን ብር  የወጭ እና ከ 3 ነጥብ አንድ  ቢሊዮን ብር በላይ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች በድምሩ ከ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ  ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዛቸውን አንስተዋል ።

የአፈፃፀም ሥልቱ  ተለዋዋጭነት  ፣ በየደረጃው ካለው  የፀጥታ ተቋማት  ጋር ያለው ቅንጅታዊ ሥራ  ጠንካራ አለመሆን እና ወቅቱን የሚመጥን አደረጃጀት አለመከተል የኮንትሮባንድ ዝውውርን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያጋጠሙ ግንባር ቀደም ችግሮች መሆናቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል ።

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን  የኮንትሮባንድ  መከላከል ድንበር ቁጥጥር እና ትራንስፓርት ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኮሚሽነር አይሻ ቶላ በኩላቸው፤ ኮንትሮባንድን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ የነበረው ቅንጅታዊ ሥራ አበረታች መሆኑን ገልፀው ድርጊቱ   በታጠቁ ኃይሎች ጭምር የሚፈፀም በመሆኑ  እርሱን መመከት የሚያስችል  የህግ ማስከበር ዘመቻ ማካሔድ  እንደሚገባ አስረድተዋል።

"የኮንትሮባንድ ወንጀል የህዝብን  እና የሃገርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል  ነው " ያሉት ኮሚሽነሩ  የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ድርጊቱን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሚያስችል መልኩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል::

በውይይቱ ኮንትሮባንድን በመከላከል እና በመቆጣጠር ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በቀጣይ ወራት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ቅንጅታዊ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል  እንደሚገባቸው መግባባት  ላይ ተደርሷል ::

Asset Publisher

Asset Publisher

ዜና

  • ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Fri, 8 Mar 2024
ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
  • ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Tue, 27 Feb 2024
ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
  • ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Wed, 21 Feb 2024
ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

ጠቃሚ መረጃዎች