ኮሚሽኑ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት 176 ሺህ መጻህፍትን አበረከተ

Search Results

Nested Applications

Asset Publisher

null ኮሚሽኑ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት 176 ሺህ መጻህፍትን አበረከተ

ኮሚሽኑ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት 176  ሺህ  መጻህፍትን አበረከተ
*****************************************
 “አንድ ሚሊዮን መጻህፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ“ በሚል መሪ ቃል አንድ ሚሊዮን መጻህፍት ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ለማሰባሰብ የተደረገውን ጥሪ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን   በዛሬው ዕለት የተለያዩ ይዘት ያላቸውን 176 ሺህ መጻህፍትን አስረክቧል።
በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ ፕሬዝደንት ክብርት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፤ የተማረ የተመራመረ ትውልድ ለመፍጠር የቤተመጻህፍት ሚና  አይተኬ መሆኑን ገልጸው፣ ይህንን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ሁሉም ዜጋ ለቤተመጻህፍቱ መጻህፍትን እንዲያበረክት ጠይቀዋል ። የጉምሩክ ኮሚሽን ላደረገው ድጋፍም ፕሬዝዳንቷ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወ/ሃና በበኩላቸው ፤ አብርሆት ቤተመፃህፍትን የተለየ እና የተደራጀ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ለአንድ ወር በሚቆየው በዚህ የመጻህፍት ማሰባሰብ መርሃ ግብርም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት እና መጻህፍቱን ያስረከቡት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ ”ይህንን ትልቅ ሃገራዊ ጥሪ ተቀብለን የዚህ ታሪክ ተካፋይ በመሆናችን ድርብ ክብር  ይሰማናል” ሲሉ ገልፀዋል።
ኮሚሽነር ደበሌ አክለውም፣ ኮሚሽኑ ከአሁን በፊት 1.4 ሚሊዮን መጻህፍትን ለአብርሆት ቤተመጻህፍት መለገሱን አስታውሰው መጻህፍት ትውልድን የሚገነቡ እና  የሚያንጹ በመሆናቸው ኮሚሽኑ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን  ለቤተመጻህፍቱ  ላደረገው ድጋፍም የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡

 

Asset Publisher

Asset Publisher

ዜና

  • ከ161 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Tue, 30 May 2023
ከ161 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
  • አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የታክስ እና የጉምሩክ አምባሳደሮች ሆነው ተሰየሙ Tue, 2 May 2023
አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የታክስ እና የጉምሩክ አምባሳደሮች ሆነው ተሰየሙ
  • ግብር ለሀገር ክብር በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው የታክስ እና የጉምሩክ ህግ ተገዥነት ንቅናቄ የታክስ መሰረትን ለማስፋት፣ የአሰራር ስርዓትን ምቹ ለማድረግ ብሎም የህግ ተገዥነት ዓቅምን ለማሳደግ ይረዳልߴߴ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ Tue, 2 May 2023
ግብር ለሀገር ክብር በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው የታክስ እና የጉምሩክ ህግ ተገዥነት ንቅናቄ የታክስ መሰረትን ለማስፋት፣ የአሰራር ስርዓትን ምቹ ለማድረግ ብሎም የህግ ተገዥነት ዓቅምን ለማሳደግ ይረዳልߴߴ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

ጠቃሚ መረጃዎች