ኮሚሽኑ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት 176 ሺህ መጻህፍትን አበረከተ

搜索结果

内嵌的应用

资产发布器

null ኮሚሽኑ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት 176 ሺህ መጻህፍትን አበረከተ

ኮሚሽኑ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት 176  ሺህ  መጻህፍትን አበረከተ
*****************************************
 “አንድ ሚሊዮን መጻህፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ“ በሚል መሪ ቃል አንድ ሚሊዮን መጻህፍት ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ለማሰባሰብ የተደረገውን ጥሪ ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን   በዛሬው ዕለት የተለያዩ ይዘት ያላቸውን 176 ሺህ መጻህፍትን አስረክቧል።
በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ ፕሬዝደንት ክብርት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፤ የተማረ የተመራመረ ትውልድ ለመፍጠር የቤተመጻህፍት ሚና  አይተኬ መሆኑን ገልጸው፣ ይህንን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ሁሉም ዜጋ ለቤተመጻህፍቱ መጻህፍትን እንዲያበረክት ጠይቀዋል ። የጉምሩክ ኮሚሽን ላደረገው ድጋፍም ፕሬዝዳንቷ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወ/ሃና በበኩላቸው ፤ አብርሆት ቤተመፃህፍትን የተለየ እና የተደራጀ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ለአንድ ወር በሚቆየው በዚህ የመጻህፍት ማሰባሰብ መርሃ ግብርም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት እና መጻህፍቱን ያስረከቡት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ ”ይህንን ትልቅ ሃገራዊ ጥሪ ተቀብለን የዚህ ታሪክ ተካፋይ በመሆናችን ድርብ ክብር  ይሰማናል” ሲሉ ገልፀዋል።
ኮሚሽነር ደበሌ አክለውም፣ ኮሚሽኑ ከአሁን በፊት 1.4 ሚሊዮን መጻህፍትን ለአብርሆት ቤተመጻህፍት መለገሱን አስታውሰው መጻህፍት ትውልድን የሚገነቡ እና  የሚያንጹ በመሆናቸው ኮሚሽኑ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን  ለቤተመጻህፍቱ  ላደረገው ድጋፍም የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡

 

资产发布器

资产发布器

ዜና

  • ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ 星期五, 8 三月 2024
ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
  • ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ 星期二, 27 二月 2024
ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
  • ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ 星期三, 21 二月 2024
ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

资产发布器

内嵌的应用

资产发布器

ጠቃሚ መረጃዎች