ከ255 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ እጽ እና ሌሎች የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ::

Search Results

Nested Applications

Asset Publisher

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ264 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Fri, 8 Mar 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Tue, 27 Feb 2024

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Wed, 21 Feb 2024

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡

ኮሚሽኑ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ97 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቧል፡፡ Mon, 12 Feb 2024

Asset Publisher

Asset Publisher

null ከ255 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ እጽ እና ሌሎች የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ::

    የጉምሩክ ኮሚሽን ከጥቅምት 18 ቀን እስከ 24 /2015 ዓም  ባደረገው ክትትል 144 ነጥብ 8 ሚሊዮን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 195 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የወጭ በአጠቃላይ 339 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ  ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ  ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በተጠቀሱት ቀናቶች ውስጥ 24 ነጥብ 1 እና 8 ነጥብ 2 ኪ.ግ  የሚመዝን ግምታዊ ዋጋው ከ255 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ  ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ እጽ በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሀገር ሊወጣ  እና ሊገባ ሲል  በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ባለፉት ሰባት ቀናት የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን ጨምሮ  በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣  ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት   እና የተለያዩ  ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አዲስ አበባ ኤርፖርት ፣ ጅግጅጋ  ፣ እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 73 ነጥብ 4 ሚሊዮን ፣ 15 ነጥብ 9 ሚሊዮን እና 13  ነጥብ 9  ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል  ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 11 ግለሰቦች እና 36 ኮንትሮባንድ ጭነው የተገኙ ተሽከርካሪዎች  በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaCustomsCommission

 

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

ጠቃሚ መረጃዎች