ከ168 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Search Results

Nested Applications

Asset Publisher

ሙስና፤ ሀገራዊ ወጭን በሀገራዊ ገቢ ለመሸፈን የያዝነውን እቅድ ለማሳካት የምናደርገውን ጥረት የሚፈትን በመሆኑ የጸረ ሙስና ትግሉን አጠናክረን እንቀጥላለን ፡- የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ

ሙስና፤ ሀገራዊ ወጭን በሀገራዊ ገቢ ለመሸፈን የያዝነውን እቅድ ለማሳካት የምናደርገውን ጥረት የሚፈትን በመሆኑ የጸረ ሙስና ትግሉን አጠናክረን እንቀጥላለን ፡- የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ Mon, 4 Dec 2023

አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 መሸጋገሪያ ድንጋጌ አንቀፅ 43(3) መሰረት አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ እቃዎች ላይ የኤክሳይስ ታክስ የሚሰላው እና የሚሰበሰበው በነባሩ አዋጅ ቁጥር 307/1995(እንደተሻሻለው) እንደሆነ ተገልጿል፡፡

አዲሱ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 መሸጋገሪያ ድንጋጌ አንቀፅ 43(3) መሰረት አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ እቃዎች ላይ የኤክሳይስ ታክስ የሚሰላው እና የሚሰበሰበው በነባሩ አዋጅ ቁጥር 307/1995(እንደተሻሻለው) እንደሆነ ተገልጿል፡፡ Sat, 25 Nov 2023

ከ284 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ284 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Wed, 22 Nov 2023

ከ343 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ343 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Tue, 7 Nov 2023

Asset Publisher

Asset Publisher

null ከ168 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከታህሳስ 28 ቀን እስከ ጥር 4/2015 ዓ.ም  ባደረገው ክትትል 86 ሚሊዮን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 82 ነጥብ 6ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 168  ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ  የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ  ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣  ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት   እና የተለያዩ  ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አዋሽ፣ ድሬድዋ እና አቃቂ ቃሊቲ  ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 37 ነጥብ 9  ሚሊዮን፣ 13 ነጥብ 8  ሚሊዮን እና 10   ሚሊዮን  ብር  በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ 12 ግለሰቦች እና ስድስት  ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaCustomsCommission

 

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

ጠቃሚ መረጃዎች