የናይጀሪያ መንግስት ልኡካን ቡድን በጉምሩክ ኮሚሽን የልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት አካሄዱ

Search Results

Nested Applications

Asset Publisher

ከ161 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ161 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Tue, 30 May 2023

አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የታክስ እና የጉምሩክ አምባሳደሮች ሆነው ተሰየሙ

አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የታክስ እና የጉምሩክ አምባሳደሮች ሆነው ተሰየሙ Tue, 2 May 2023

ግብር ለሀገር ክብር በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው የታክስ እና የጉምሩክ ህግ ተገዥነት ንቅናቄ የታክስ መሰረትን ለማስፋት፣ የአሰራር ስርዓትን ምቹ ለማድረግ ብሎም የህግ ተገዥነት ዓቅምን ለማሳደግ ይረዳልߴߴ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ

ግብር ለሀገር ክብር በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው የታክስ እና የጉምሩክ ህግ ተገዥነት ንቅናቄ የታክስ መሰረትን ለማስፋት፣ የአሰራር ስርዓትን ምቹ ለማድረግ ብሎም የህግ ተገዥነት ዓቅምን ለማሳደግ ይረዳልߴߴ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ Tue, 2 May 2023

ከ258 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ258 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ Sat, 29 Apr 2023

Asset Publisher

Asset Publisher

null የናይጀሪያ መንግስት ልኡካን ቡድን በጉምሩክ ኮሚሽን የልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት አካሄዱ

የናይጀሪያ መንግስት ልኡካን ቡድን በጉምሩክ ኮሚሽን የልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት አካሄዱ
**********************
የናይጀሪያ ጉምሩክ አገልግሎትን ጨምሮ ከተለያዩ  ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ  የልኡካን ቡድን አባላት በጉምሩክ ኮሚሽን  በመገኘት የልምድ ልውውጥ ያካሄዱ ሲሆን የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን የስራ እንቅስቃሴም ተመልክተዋል፡፡
የልኡካን ቡድኑ በጉምሩክ ኮሚሽን አገልግሎቱን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የተሰሩት ስራዎች አበረታች እና ተጨባጭ ልምድ ያገኙበት መሆኑን ጠቁመው በዋናው መስሪ ቤት እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የስራ ከባቢን ምቹና ማራኪ ለማድረግ የተሰራው ስራም  በተሞክሮነት የሚወስዱት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የልኡካን ቡድኑ አክለውም፣ ኮሚሽኑ ወረቀት አልባ አገልግሎትን በመተግበሩ ለደንበኞች በየትኛውም ሁኔታ እና ጊዜ አግልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ፣ ኮሚሽኑ በከፍተኛ የለውጥ ግስጋሴ ላይ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የናይጀሪያ መንግስት ልኡካን ቡድን በሁለት ቀን ቆይታቸው  የአዲስ አበባ ኤርፖርት እና በሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን የጎበኙ ሲሆን የልምድ ልውውጡ ተግባራዊ የሆኑ እውቀቶችን የቀሰሙበት እና  ስኬታማ እንደነበርም  ገልጸዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን የኮሚሽኑ የለውጥ አማካሪ አቶ መንግስቱ ተፈራ በበኩላቸው፣ በኮሚሽኑ  ባለፉት ሶስት ዓመታት መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው በቀጣይም የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ የሚያዘመኑን ኮሚሽኑን ብቁ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Untitled Basic Web Content

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

ጠቃሚ መረጃዎች